Zemare App Icon
Main Image
book

የተሰቀለው በጳውሎስ ፈቃዱ

850 ETB

Quantity

1

የኢየሱስ ሞት እጅግ ዝነኛ ሞት ነው። በዓለም ላይ እንደዚህ የተነገረለት ሞት የለም። በዚህ ደረጃ የታወቀ፣ የበርካታ የሥነ ጥበብ መስኮች (ሥዕል፣ ሙዚቃ፣ ቲአትር፣ ፊልም፣ ቅርጻ ቅርጽ፣ ወዘተ.) ጭብጥ እና እጅግ መወያያ የሆነ ሞት የለም። ስፍር ቍጥር የሌላቸው መጻሕፍትም ተጽፈውበታል። ይህን መስቀል ልዩ የሚያደርገው በዚያ ላይ የተሰቀለው ሰው ማንነት ነው። አምላክ በሥጋ የተሰቀለበት መሆኑ። እርሱን የሚመስል ሰው ኖሮ አያውቅም። በምድር ላይ እንደ እርሱ ንጹሕ፣ እንደ እርሱ ቅዱስ፣ እንደ እርሱ ደግ፣ እንደ እርሱ ትሑት፣ እንደ እርሱ ጻድቅ፣ እንደ እርሱ ቸር ሰው ኖሮ አያውቅም። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እንደ እርሱ ዐይነት መልካም ኖሮ አያውቅም። ሊሰቀል ያልተገባው ቅዱስ ሰው ነው የተሰቀለው። "የተሰቀለው" ገጽ 12።